ባጠቃላይ
ለ ሰንጠረዥ ሰነዶች ባጠቃላይ ማሰናጃዎች መግለጫ
መነሻዎች
የ መለኪያ ክፍል
የ መለኪየ ክፍል በ ሰንጠረዥ ውስጥ መወሰኛ
ማስረጊያ ማስቆሚያ
የ ማስረጊያ ማስቆሚያ እርቀት መወሰኛ
ማስገቢያ ማሰናጃዎች
የ ተመረጠውን ለ ማንቀሳቀስ ማስገቢያውን ይጫኑ
መጠቆሚያው በ ሰንጠረዥ ውስጥ በ ምን አቅጣጫ እንደሚንቀሳቀስ መወሰኛ እርስዎ ማስገቢያ ቁልፍ ከ ተጫኑ በኋላ
ወደ ማረሚያ ዘዴ ለመቀየር ማስገቢያውን ይጫኑ
እርስዎን ወዲያውኑ እንዲያርሙ ያስችሎታል የ ተመረጠውን ክፍል የ ማስገቢያ ቁልፍ ከ ተጫኑ በኋላ
አቀራረብ ማስፊያ
ራሱ በራሱ መፈጸሚያ የ አቀራረብ መለያ መወሰኛ ለ ተመረጠው ክፍል ወደ ባዶ አጓዳኝ ክፍሎች ለምሳሌ: የ ተመረጠው ክፍል ይዞታዎች የ ማድመቂያ መለያ አላቸው: ይህ የ ማድመቂያ መለያ መፈጸሚያ በ አጓዳኝ ክፍሎች ውስጥ: ቀደም ብሎ የ ተለየ አቀራረብ ያላቸው ክፍሎች አይሻሻሉም በዚህ ተግባር: እርስዎ መመልከት ይችላሉ የ ጥያቄዎችን መጠን በ መጫን የ ትእዛዝ Ctrl + * (የ ማባዣ ምልክት በ ቁጥር መምቻ ገበታ ላይ) አቋራጭ: ይህ አቀራረብ ይፈጸማል ለ ሁሉም አዲስ ዋጋዎች ለሚገቡ በዚህ መጠን ውስጥ: መደበኛው ነባር ማሰናጃ ይፈጸማል ለ ክፍሎች ከ መጠኑ ውጪ ላሉ
አዲስ አምዶች/ረድፎች በሚገቡ ጊዜ ማመሳከሪያውን ማስፊያ
ማመሳከሪያዎች ይሰፉ እንደሆን መወሰኛ አምዶች እና ረድፎች በሚገቡ ጊዜ ከ ማመሳከሪያው መጠን አጓዳኝ: ይህ የሚቻለው የ ማመሳከሪያው መጠን: አምድ ወይንም ረድፍ ሲገባ ነው: በ መጀመሪያ ቢያንስ የ ሁለት ክፍሎች እርቀት በሚፈለገው አቅጣጫ ሲኖር ነው
ለምሳሌ: ይህ መጠን ከሆነ A1:B1 በ መቀመሪያ የ ተገለጸው እና እርስዎ ማስገባት ከ ፈለጉ አዲስ አምድ ከ አምድ B, በኋላ: መግለጫው ይሰፋል ወደ A1:C1. ይህ መጠን ከሆነ A1:B1 ይገለጻል እና አዲስ ረድፍ ይገባል ከ ረድፉ ስር 1: መግለጫው አይሰፋም: አንድ ነጠላ ክፍል ብቻ በ ቁመት አቅጣጫ ስላለ
እርስዎ ረድፎች እና አምዶች ካስገቡ በ መግለጫው መካከል ቦታ: መግለጫው ሁልጊዜ ይሰፋል
የ ተመረጠውን የ አምድ/ረድፍ ራስጌዎች ማድመቂያ
በ ተመረጡት አምዶች እና ረድፎች ውስጥ የ አምድ እና የ ረድፍ ራስጌዎች ይደምቁ እንደሆን መወሰኛ
ለ ጽሁፍ አቀራረብ የ ማተሚያ መለኪያ ይጠቀሙ
የ ማተሚያ መለኪያ ይፈጸም እንደሆን መወሰኛ በ ማተሚያው ላይ እና በ መመልከቻው ማሳያ አቀራረብ ላይ እዚህ ሳጥን ውስጥ ምልክት ካልተደረገበት: የማተሚያ ነፃ እቅድ ይጠቀማል ለ መመልከቻ ማሳያ እና ለማተሚያ
ዳታ በሚለጠፍ ጊዜ በ ላዩ ላይ ደርቦ መጻፊያ ማስጠንቀቂያ ማሳያ
እርስዎ ክፍሎች ከ ቁራጭ ሰሌዳ ውስጥ ወደ ባዶ ያልሆነ የ ክፍል መጠን በሚለጥፉ ጊዜ: የ ማስጠንቀቂያ መግለጫ ማሳያ